Telegram Group Search
እድሜዋንም አፈቀርኩት
(ካሊድ አቅሉ)


“እድሜሽ ስንት ነዉ አልኳት ?” ያላሰበችዉ ድንገተኛ ጥያቄ አይንዋን ሰብራ መሬት መሬት አየች ለጠቅላላ እዉቀት ነበር አጠያየቄ ግንባርዋ ሰላሳዎቹን እንደተሻገረ ያሳብቃል ከሂጃብዋ ሾልከዉ የወጡ አንዳንድ የፀጉር ዘለላዎች በትንሹ ሽበት ጀምሮዋቸዋል ። ዉብ ናት እኮ ! ልብዋ አፍላ ወጣት ነዉ ሳትሰስት ታፈቅራለች ለዛ ነዉ ሚጥላት የበዛዉ ።

ያን ትልቅ አይንዋን ቀና አድርጋዉ ከሀሳብ ከሄደችበት ተመልሳ “ ገምት እስኪ “ አለቺኝ እኔም ማወቄን ለመደበቅ “እእ…”አልኩኝና “ ሀያዎቹ መጨረሻ አካባቢ አንደደረስኩበት ነገር እጄን እያወዛወዝኩ “

“ ሰላሳ አንድ አመቴ ነዉ” አለቺኝ እጆችዋን እያሻሸች ከእድሜዋ በላይ የእጅዋ ዉበት ወስዶኛል መልስ ሳልሰጣት ቆየዉ “ ምነዉ?” ስትለኝ ከሀሳቤ ነቃዉና “ ዉይ ምን አላት ታድያ ገና እኮ ነሽ አልኳት“ “ ተዉ እንጂ “ “ የምር ስንት ፈጣሪ የፃፈልሽ ግን ያልገለጥሽዉ ኖረሽ ምታልፊዉ የህይወት ገፅ አለ ብቻ አንቺ ተስፋ ሰንቂ” አልኩኝ። ነገሩ ፍቅር አነቃቂ አይደለም አስደናቂ ነገሮች ያናግር የለ እንደዉም እድሜዋንም አፈቀርኩት ! 31 ቁጥር ባስ 31 ቁጥር ጫማ 31 ቁጥር ሱሪ በቃ 31 ቁጥር ምንም ሆነ ይበቃኛል አለ አይደል ሰዉ ነግሪዉ አለሰማ ሲል “31 ጊዜ ነገርኩህ አይደል !” ሚያስብል ሁሉንም ያስገኘ ሁሉም ያሳጣ ፍቅር ።
ስሞት ሀዉልት ሚሰራልኝ
ቆሜ ብድር ከለከለኝ
ሀበሻ ይወዳል ከበድን መታገል
ሲሸሹ መነጠፍ ሊቀርብ ሲል
ማግለል !

( ካሊድ አቅሉ)
የተፋቼዎች ወግ
( ካሊድ አቅሉ)


ጋዜጠኛ ፦” ለምን ተዉካት “

ባል ፦ “ስለማምናት !”

ጋዜጠኛ ፦ “ ማለት ?”

ባል ፦ “ ምግባርዋን መጠራጠር አልችልም ያሳየችንን አመንኩት።”

ጋዜጠኛ ፦ “ማፍቀር ምን ማለት ነዉ ?”

ባል ፦ “ ማፍቀር ማለት ያን ሰዉ ማንገስ ብቻ አይደለም አንዳንዴም ማርከስ አለዉ በልብህ ጥባጥቤ ለመጫወት የተዘጋጁትን ከሜዳህ አርቃቸዉ ያኔ አንተነትህ ይከበራል።”

ጋዜጠኛ ፦ “ያፈቀረ ሁሉ ነገሩን ይሰጣል ይባላል ?“

ባል ፦ “አዎ ይሰጣል ግን ከተጃጃለ ይ'ሰጣል !“

ጋዜጠኛ ፦ “መጃጃል ስትል ?”

ባል ፦ “እሱን ጅል አፍቃሪ ስትሆን ነዉ ሚገባህ !”

ሚስትየዉ መሬት መሬት አየች ።
ፍቅር ከሞላበት የትም ሁን ይመቻል
ፍቅር ከሞላበት የትም ሁን ይመቻል
ፍቅር የጎደለው አለም ይሰለቻል

ሰበቤ
( ሚካያ በሀይሉ )
የምትይኝን ቃል መቼ አቆምኩኝ
መስማት
ትርጉሙ ነዉ የጠፍኝ!
ፈረሱ እየሞተ በጋሪዉ መጣላት

(ካሊድ አቅሉ)
የምር አንድ ሁለት ሶስት
( ካሊድ አቅሉ)


ሙከራ አንድ ሁለት ሶስት ማይክ ላይ እንጂ ህይወት ላይ አይሰራም። ከኖርን አይቀር የምር መኖር የምር መውደድ የምር መቅረብ ያኔ ፏፏቴዉ ያርሰናል ። ወጨፎ ያበሰብሰናል እንጂ መቼ ያጠራል።

ይሄ ሁሉ ዉጣ ወረድ እንኳን ተወለድክ ላላቹኝ ምስጋና ለማሻገር ነዉ እድሜ የጨመረልኝ የምር እንድኖር ሽቶ ነዉና የምር እንድ ሁለት ሶስት ብያለዉ 🙏🙏🙏
ሲጠቅሱት ማይገባዉ
( ፍቅር )

ካሊድ አቅሉ


እኔ ጋር የረሳችዉን መፅሀፍ ልሰጣት እንዳገኘዋት የእጆችዋን ጥፍሮች አየዋቸዉ ከበቂ በላይ ተከርክመዋል ። ድምፄን ዝግ አድርጌ “ጥፍርሽን መብላት ጀመርሽ አይደል ?”አልኳት እሷም የመፃሀፉን ሽፍን ትክ ብላ እያየች “ አዎ ሲያድግ አንተን እያስታወሰ አስቸገረኝ ከዚህ ሁሉ ብዬ ወደ ቀድሞ ልምዴ ተመለስኩኝ !” አለች መጨለም መቆጣት እና ፊት መንሳት ማይችለዉን ፊትዋን ያቅሟን ለማደብዘዝ እየሞከረች።

ልብዋ ከኔ ለመሸሽ ያቅሙን እያረገ እንዳለ ያኔ ተረዳዉ ጥፍርዋን በጥርሷ ልጣ ከአፍዋ እንደተፋችዉ ፍቅሬን አንቅራ ለመትፋት ዳር ላይ እንዳለች ተገለጠልኝ ። ልምዶች ለካ መዉደዳችንን ይገልፃሉ ወፍራም ሴት ወዳለዉ ያልኩትን ይዛ ይሄኔ ለመክሳት ጂም መስራት ጀምራለች ፍቅር በትግል ሚወጣ መስልዋት …..


ከዛ ቀን ብሃላ አላገኘዋትም ምን ትምሰል ምን አላዉቅም ምወዳቸዉን ነገሮችዋን ለማርገፍ ስትታገል ይባስ እያጌጠች ይሆናል ደግሞ እንደፍቅር ማን አለ እልህኛ ሊቀድሙት በሮጡ ቁጥር በአቆራጭ መንገድ ካለንበት ሚደርስ ሲጠቅሱት ማይገባዉ ፍራ !
Forwarded from ካሊድ አቅሉ
የወንዝ ዳር ድንጋይ አምነው
የማይረግጡሽ
ለማለፍ ባትሆኚ ለጌጥነት አጩሽ !

( ካሊድ አቅሉ)
“በቃ አልኖርም ሳመነታ
ላጉል ፍቅር ስቃይ ለገዳይ ትዝታ
በኔ የሳቀች ጥርስ ትከደናለች
ይብላኝ እንጂ ላንቺ ነፍሴስ
ታመልጣለች ! “

“አትስቂም በፍረቴ”

ኤልያስ መልካ በልዑል ሀይሉ በኩል ካሻገረልን ድንቅ ሀሳቦች መሀል አንዷ ናት እቺ ስራ አድምጥዋት
ከወራጁ ከዛ ድፍርስ ሳያጠሉት
የተቀዳ
ችሎት ቶመዉ ማይሞግቱት
መቀበል ነዉ ከባድ እዳ !


( ካሊድ አቅሉ)
አንዳንዱ እንደዚህ የሰከነ ልብ ይታደላል እኔ ጭሬ ልበትነዉ ስለነገ ከሌለዉበት ምን አገባኝ አይቼ እንዳላየ ባልፈወስ ብሎ የምን አገባኝን መንገድ በሚመርጥበት ዘመን ዙበይዳ የምር ሰዉ ሆና ተገኝታለች ! እረፍት ቀናቹን እስኪ ጎራ ብላቹ ዘይርዋት ሀይማኖት ብሔር ሳትለይ በንፁህ መንፈስ ትዉልድ ለማዳን እየተጋች ነዉ ።

እስልምና ጉዳዮች ዋና ፅህፈት ቤት መገኛዋ ነዉ የበለጠ መረጃ ካሻቹ በውስጥ አውሩኝ @kalu30
"የሰዎችን ጥፋት እንደ ጌታ ሆናቹ:የራሳችሁን ጥፋት እንደ ባርያ ሆናቹ አትመልከቱ:በወንጀል የተፈተኑ ሰዎችን ስታዩ እዘኑላቸው:አሏህ ከዛ ስለጠበቃችሁም አመስግኑት"
                           ኢማሙ ማሊክ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ግጥሜን እስኪ በመቅዲ አንደበት ስሙት በሴት ሲሆን የሆነ ዉበት አለዉ 🥰🥰🥰🥰🥰 ( በምን ብፀድቅ ነዉ? )
ልቤን ገልጫለዉ
( ካሊድ አቅሉ)


አውቃለዉ ትርፍሽ ነኝ
ባሻሽ ምታገኚኝ
ለዛም አይደል ዉዴ ደርሰሽ
ምታቀይኝ ፥


አቤትም ሳበዛ መሄጃ እንደሌለዉ
በመልክሽ ስቆጠር
መሄድ አደረሰኝ የመቁረጦች
ሀገር !


አሁን ብዙ አትልፊ
በቃል አትስነፊ
በቀንሽ ነቅቼ
ልቤን ገልጫለዉ
ማፍቀር ህይወት
አይደል ሁለት ገፅ አለዉ ።
ዉስጤ ቂምን ሺሸርብ
ምህረት ከቦታዉ ይድረስ

መዉደድ አለዉ ሚታይ መልክ
ማፍቀር አለዉ ትልቅ መልስ !


( ካሊድ አቅሉ)
ቢሰፍሩሽ ቢሰፍሩሽ
ሞልተሽ የምትፈሺ
አዎ አንቺ እኮ ነሽ
ከልጅሽ ደሴት ላይ
መኖር ምትቀድሺ ፣

አዎ ግብርሽ እኮ ነዉ
በመስጠት በርትተሽ
መቀበል ምትረሺ !

(ካሊድ አቅሉ)


የኔ ወብ እናት እንኳን ተወለድሺልኝ መፈጠርሽ ፈጥሮኛል ምቾቴ 🎂🎂🎂❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
Forwarded from ባ ይ ራ | Bayra
ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 1.pdf
3 MB
ባይራ ዲጂታል መጽሔት



ቅጽ ሁለት ቁጥር አንድ




በእነዚህ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!


ቴሌግራም- https://www.tg-me.com/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital
ቲክቶክ (TikTok) https://www.tiktok.com/@bayramedia?_t=8r47KnYX7cz&_r=1

ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ

ኢ-ሜይል- [email protected]

ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!
ክፋትን ስሎ
( ካሊድ አቅሉ)


ጥቃቅን እድሜ
የእንባ ጠብታ
ሰቅዞ ይዞኛል
ፈጥሮ ትዝታ

መኖር በዉሉ ልክ
እንደ ክራር ሳይደረደር
ልቤ ይመኛል ሚወደዉ ልብ
ውስጥ ገብቶ ለማደር !

አይሙላልህ ያለዉ ከቀዪ
አድባሩ የተኳረፈ
ሲያምር ይላል ከቁንጅናዉ
ስር እየረገፈ

በሳቅም በኩል በአለዉ
መቃኛ
በምሽቴ ላይ በቀን ስተኛ
ስንቱ አሳለፈኝ
ስንቱ ቀጠፈኝ

በሸንጋይ ቃላት እያታለለ
ወዳጄ መስሎ
ልደነቅ አለ ነጭ ሸራ ላይ
ክፋትን ስሎ ።
2025/05/12 08:27:57
Back to Top
HTML Embed Code: